የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አድራሻ ለውጥ አደረገ

የመጋቢት መድሃኒ ዓለምን ክብረ በዓል እሁድ መጋቢት ፳፭ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. (5 አፕሪል 2019) ተከብሮ ዋለ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በኔዘርላንድ፤ በየዓመቱ የሚከበረው የጌታችንና መድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ መታሰቢያ የሆነውን የመጋቢት መድሃኒ ዓለምን ክብረ በዓል እሁድ መጋቢት ፳፭ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. (5 አፕሪል 2019) ከጥዋቱ ፪ ሰዓት (8:00 AM) ጀምሮ ፔርኒስ-ሮተርዳም በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከተለያዩ አድባራት በመጡ አባቶች ካህናት፣ ወንድሞች ዲያቆናት እና ምዕመናን በቅዳሴና ታቦት በማንገስ በዓሉ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውልሏ። 
በተጨማሪም ቤተ መቅደሱን በአዳዲስ የቅዱሳን ስዕላት በማስዋብ ክብረ በዓሉ የበለጠ ድምቀት እንዲያገኝ ምዕመኑ በታላቅ ትጋት ሲያገዝ ሰንብቷል። የበዓሉን አከባበር የፎቶ ቅንብር ከዚህ በታች ይመልከቱ።  

ለተጨማሪ ፎቶዎች እዚህ ላይ ይጫኑት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት በኔዘርላንድ

Share by: